THREAD: በሊባኖስ ሀገር ትሰራ የነበረቿ ወጣት ኢትዮጵያዊት ሌንሳ ለሊሳ ታሪኳ በምዕራባውያንና የአረብ ሀገር መገናኛ ብዙሃን ብዙ ቢዘገብም በኢትዮጵያዊያን ብሱ ስላልተሰማ ይዤላችሁ እቀርባለሁ። ታዋቂው የፋሽን ኩባንያ @Eleanorecoutureን የሚነካ ነው።

የ22 አመቷ ሌንሳ ለሊሳ ቱፋ ለስራ ወደ ሊባኖሱ ዋና ከተማ ቤሩት ታመራለች። እንደ ብዙ ኢትዮጵያዊያን እህቶቻችን በተቀጠረችበት ቤት ለተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰት ትጋለጣለች። ደሞዝ በሰነሰርኣቱ አይከፈላትም፣ ቤት ተቆልፎባት ትደበደብ ነበር።
በፈረንጆች አቆጣጠር ማርች ወር 2018 አመልጣለሁ ብላ ከቤቱ 2ኛ ፎቅ ትዘላለች። ነፍሷ ቢተርፍም ሁለቱ እግሮቿ ስለተሰበሩ ማምለጥ ሳትችል ቀረች፣ ሆስፒታል ትገባለች። በዛን ወቅት የሌንሳ ቤተሰቦች ስለ ሁኔታዋ ያለውን ለነ @ThisIsLebanonDW ያካፍላሉ።
የቤሩት ነዋሪ የሆኑት የሌንሳ አክስት ወዘሮ ገነት ሞሲሳ ሌንሳ ወዳለችበት ሆስፒታል ሄዳ የስልኳን ካሜራ በመጠቀም ሌንሳ ስለሚደርሳት በደል እንድታካፍላት ታደርጋለች። በ5 ደቂቃው ቪዲዮ ስለ አሰሪዎቿና ስለሚያደርሱባት በደል ለአክስቷ ትናገራለች።
የሌንሳ አሰሪዎች ከታወቁ የሊባኖስ ባለሃብቶች የሆኑት የአጃሚ-ኻሊል (Ajami-Khalil) ቤተሰብ የተወለዱ ናቸው። ብዙ ንብረት ያከማቹና ዝነኛው የ@Eleanorecouture የፋሽን (haute couture) ኩባንያ ባለቤት ፎቶ ላይ ያሉት ኤሌኖር አጃሚ (Eleanore Ajami) ይባላሉ።
ኤሌኖር 3 ልጆች አሏቸው። 3ቱም የ @Eleanorecouture ድርጅት በሞዴሊንግና በተለያዩ ስራዎች ያገለግላሉ። ሌንሳ እንዳስረዳችው በ4ቱ ትደበደብ እንደነበርና ሴት ልጆቹ ፀጉሯን በመጎተት ወንዱ አይኖቿን በጣቶቹ በመውጋት ይጎዷት እንደነበርም ተናገረች።
@Eleanorecouture ድርጅት በሆሊዉድና በመላው አለም እውቅና ያተረፈ ታላቅ ኩባንያ ነበር። ጉዳቸው በ @ThisIsLebanonDW ሲጋለጥ በዝናቸው ምክንያት ታሪኩ በጣም ተሰሚነት አግኝቶ ብዙ ሰውን በወቅቱ አስደንግጧል።
የእንግሊዙ @DailyMailUK ታሪኩን በዚህ መልክ ዘገበ። የሌንሳ ቪዲዮ ከሚሊዮን ግዜ በላይ ታይቶ በሊባኖስ ህብረተሰብ የቤተሰቡ ጉድ የመነጋገርያ እርዕስ ሆነ። https://t.co/wMEW1Nk3db
በሊባኖሱ የከፈላ ህግ አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ያለአሰሪዎቿ ፍቃድ አሰሪ ማስቀየር ስለማትችል ሌንሳ ታክማ ወደመጣችበት የነ ኤሌኖር ቤት እንደምትመለስ ሲታወቅ ወደ 50 የሚሆኑ ሰዎች ቤቱ ውጪ ሄደው ሰል አደረጉ። እንድትለቀቅ ጥሩ አደረጉ።
በማህበራዊ ድረ ገፆች በተለይ በInstagram #IamLensa ወይ #FreeLensa በማለት በመላው አለም የሚገኙ ሰዎች ጥሪያቸውን አስተላልፈው የአጃሚ-ኻሊል ቤተሰቦችን አወገዙ።
ጉዳዩ እየከረረ ሲመጣና ስማቸውም የኩባንያው ንግድ እንደሚጎዳ ሲረዱት እጅግ በጣም የወረደ የህሊና የለሾች ነገር ለማድረግ ይወስናሉ። ሌንሳ ከነ ሆስፒታል አልጋዋ ቴሌቪዥን ቀርባ አሰሪዎቿ ባሉበት ስለነሱ ጥሩ ነገር እንድትናገር ትገደዳለች።
በአልጃዲድ ጣቢያ የተላለፈው የቴሌቪዥን ስርጭት ብዙዎችን አስቆጣ። Boycott ተጀመረ። ዝነኛ ፊልም ሰሪዎችና አርቲስቶች በተለይ ዝነኛዋ አርቲስት @carrieunderwood@Eleanorecouture ጋር የነበራቸው ውል አሰረዙ።
@ThisIsLebanonDW ሌንሳ እንድትለቀቅ ቤተሰቡ ላይ ጫና አሳደሩ። ስለታሪኩ ለተከታታይ ቀናት እየዘገቡ ለጠየቃቸው ጋዘጠኛ መረጃ ሰጡ። እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ነገር ከኢትዮጵያዊ የጋዘጠኝነት ተቋም ጥያቄ አለመምጣቱ ነው።
https://t.co/IJjP5O4uDg
ኤሌኖር አጃሚ ስማችን አጠፉ በጠበቆቿ የ @ThisIsLebanonDW ድርጅት እንዲከሰስ ታደርጋለች። የድርጅቱ አመራር የሚገኘው ካናዳ ስለሆነ ብዙም አልተሳካላቸውም። በቤተሰቡ ግፊት የThis is Lebanon ድረ ገፅ ከሊባኖስ block ተደረገ።
ክስ ከቀረበባቸው መካከል የሊባኖሱ ጋዘጠኛ @timourazhari አንዱ ነበር። ቲሞር ኢትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞች የሚደርሳቸውን ግፍ በመዘገብ እውቅና ያገኘ ነው። ከመከሰሱ በፊት በፖሊስ ተይዞ ስልኩ ተቀምቶ ያለፈቃዱ ተፈትሾበታል።
ከተፈታ ቦኋላ ስለ ሌንሳ ለሊሳ በTwitter ገፁ እየፃፈ ስማችን አጠፋ ብሎ ከኤሎኖር ቤተሰብ ክስ ይቀርብለታል። ቲሞር ስራዬን ነው የሰራሁት ብሎ መልስ ምት ይሰጣል። የፍርድ ቤት ሂደቱ አልተጠናቀቀም።
https://t.co/X5DjYPldGE
አሌክሲስ ኻሊል በFacebook ገጿ ስለ ሌንሳ ስታወራ በቤሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንፅላ እራሱ ጉዳዩን መርምሮ ሌንሳ ከቤተሰቡ ምንም አይነት በደል እንዳልደረሳትና ያለአግባቡ ስማቸው እንደጠፋ ተናገረች።
ቦኋላ አክቲቪስቶች እንዳጣሩት ከኢትዮጵያዊው ቆንፅላ ምርመራ መደረጉ ተረጋገጠ። ችግሩ ግን መርማሪው የቆንፅላ ሰራተኛ ሌንሳን ያናገረ 2ቴ ነው፣ 1ኛ ግዜ አሰሪዎቿ በነበሩበት ነው፣ 2ኛው ትናገርብኛለች ብላ ሌንሳ የምትጠረጥር ልጅ ባለችበት ነበር።
@ThisIsLebanonDW አባላት እንደነገሩኝ ምርመራውን የመራውና የሌንሳን ጉዳይ በቸልተኝነት በማየትና ሄደው አናግሯት ምንም አልሆነችም ብለው ሌንሳ ወደ አሰሪዎቿ ቤት እንድትመለስ ተቃውሞ ያላሰማው የቆንፅላው ሰራተኛ አቶ አጥናፉ አስፋው ይባላሉ።
አቶ አጥናፉ የዛሬ አመት ገደማ ወደ ለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲያችን የተዘዋወረ ሲሆን አሁንም እዛው ከ @EthioEmbassyUK ተቀጥሮ እየሰራ እንዳለ የኤምባሲው ድረ ገፅ ያሳያል።
ከብዙ ግፊት ቦኋላ በAugust ወር 2018 ሌንሳ ከቤቱ ትለቀቃለችና አውሮፕላን ተሳፍራ ሀገሯ ትገባለች። ባሁኑ ሰአት ህክምናዋን በመከታተል ላይ ትገኛለች። ቤተሰቦቿ ለህክምናዋ የሚሆን በቂ ብር የላቸውም ግን ልጃቸው ከነ ነፍሷ በመመለሷ ደስተኞች ናቸው።
የካናዳ ሀገር ነዋሪው የኔፓሉ ዜጋ ዲፔንድራ ኡፕሬቲ (Dipendra Uprety) ለThis is Lebanon ድርጅት የኔፓል ልጆችን ጉዳይን የሚከታተል ነው። ከአመታት በፊት ሊባኖስ እየሰራ ደሞዜን አልተቀበልኩም ብሎ ፖሊስ ጣብያ ሲያመለክት ታስሮ 6 ወራት እስር ተቀመጠ።
ዘንድሮ አግንቼው ነበር። ከ @Interpol ለካናዳ ፖሊሶች የተላከውን ደብዳቤ አሳየኝ። በሌንሳ ጉዳይ ዲፔንድራ ተይዞ በነ ኤሌኖር ቤተሰቦች ስም ማጥፋት ክስ ከካናዳ ዲፖርት ተደርጎ ሊባኖስ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ጥያቄ ቀርቦ ነው። ካናዳ ውድቅ አደረገው።
እስካሁን ድረስ የማስፈርራርያ ደብዳቤ ከኤምባሲው ይደርሷል። ይሄኛው ከጥቂት ወራት በፊት የደረሰው ነው። የሌንሳን ጉዳይ የተከታተሉት የድርጅቱ አባል ኢትዮጵያዊያን ቢሆኑም ስማቸው ባላመታወቃቸው የተሰነዘረው ክስ በዲፔንድራ ስም ቀረበ።
Anyways...ሰውን ከማስፈራራትና ከመክሰስ ውጪ ብዙ እየሰሩ አይደሉም @Eleanorecouture። ሌንሳ ላይ ባደረሱባት ጉዳት ምክንያት ንግዳቸው ከስሯል። ከድረ ገፃቸው እንደሚታየው ለ2019 ያወጡት አዲስ የልብስ "collection" የለም።
@Eleanorecouture የFacebook ገፃቸውን አዘጉት። በInstagram የነበረው ገፃውን ከተከታዮቻቸው ውጪ ማንም እንዳያየው ወደ private የቀየሩት ስድብና ትችት ማስተናገድ ስላልቻሉ ነው። ለካናዳ ፖሊስ በተላከው ደብዳቤ መክሰራቸውን አስረዱ።
ብዛት ያላቸው መኪኖች ንብረት የነበራቸው ናቸው እነ ኤሌኖር አጃሚ። ሌንሳ በምትሰራበት ወቅት 290$ ለ8 ወራት ስራ በደሞዝ ተቀብላ ነበር። ቦኋላ የሚዲያ ሽፋኑ ሲጋነን 450$ ልካው አጠቃላው 741$ በ9 ወራት ተረከበች።
በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞች እጅግ በጣም በዝቅተኛው ከተከፈላቸው በወር ወደ 150$ ገደማ ያገኛሉ ሌሎች እስከ 200 ወይ 300 ዶላር ያገኛሉ። ሌንሳ የተቀበለችውን በሙሉ ብንወስድ በወር 85$ም አይሞላም።
ሲታገሉላት የከረሙት አክስቷ ገነት ሞሲሳ ጋር እየደወሉላት "ስማችን ማጥፋቱን ካላቆማቹ ሬሳዋን ነው የምንልክላችሁ" እያሉ ያስፈሯሯቸው እንደነበርም ለThis is Lebanon አካፍላለች።
ለማጠቃለል...ከመክሰራቸው ውጪ እነ @alexiskhalil እነ @Crystelkhalil በሙያው ምንም አይነት ኮንትራት ወይ ወደነ ሆሊዉድ የሚመልሳቸው የdesign ስራ ማግኘት እንዳልቻሉ መረዳት ችያለሁ...
ሌንሳ ለሊሳ አዲስ አበባ እየኖረች ትሰራለች። በቅርቡ እግርዎቿ ውስጥ ያለውን ብረት ለማውጣት ኦፐራሲዮን ሊያስፈልጋት ነው። በ @ThisIsLebanonDW የተመደቡላት ጠበቆች ለደሞዟም ሆኖ ለደረሰባት በደል ሁሉ የኤሌኖርን ቤተሰብ ለመክሰስ እየተዘጋጁ ነው።
ከሁሉ በላይ ሊቆሮቁረን የሚገባው ነገር ቢኖር ጉዳዩ እጅግ በጣም ተሰሚነት ያገኘ ቢሆንም ለዚህች ልጅ ካለ ጥቂት አክቲቪስቶች የደረሰላት ያገሯ ዜጋ አልነበረም። ከኔና ከሙያዬ ባልደረቦቼም ሆኖ ከሰፊው ህዝብ ሌንሳ በችግሯ ግዜ ድጋፍ አላገኘችም።
ከነበረችበት ወጥመድ ያወጧት በመላው አለም የሚገኙ የሰባዊ መብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች ናቸው። እርስ በርስ ስንባላ ወቅቱን አሳልፈነዋል። ዘንድሮ ትኩረታችን ወደ ወሳኝ ጉዳቻችን አዙረን ትርኪ ምርኪውን ለትርኪ ምርኪው ብንተወው ይበጀናል ባይ ነኝ።
ታሪኩን ለመዘገብ ወይ ልትረዷት ሃሳብ ያላችሁ ከሌንሳ ጋር ላገናኛችሁ እችላለሁ። በተጨማሪም የ@EthioEmbassyUK ሰራተኛና የደረሳት ነገር የለም ብሎ የፈረደባት የቤሩቱ ቆንፅላው አቶ አጥናፉ አስፋውም ማናገር ይቻላል።
ስለመከታተላችሁ አመሰግንሃለሁ።

More from All

You May Also Like